ክቡር አምባሳደር ሽብሩ ማሞ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳሚያ ሱሉሁ አቀረቡ።
(ሰኔ 01 ቀን 2014ዓ/ም አዲስ አበባ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ክቡር አምባሳደር ሽብሩ ማሞ የሹመት ደብዳቢያቸውን ለታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳሚያ ሱሉሁ አቅርበዋል።

አምባሰደሩ የሹመት ደብዳቢያቸውን ባቀረቡበት ወቅትም የሁለቱን ሀገራት የረጅም ዘመናት ግኑኝነትና ቀጣይ የትብብር መስኮችን በሚመለከት ከክብርት ፕሬዝዳንቷ ጋር ሀሳብ ተለዋውጠዋል ።

አምባሳደር ሽብሩ በዚህ ወቅትም በሀገሪቱ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና መንግስት እየወሰዳቸው ስላለው እርምጃ እንዲሁም ስለ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለፕሬዝዳንቷ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

በታንዛኒያ እስር ቤት በአስከፊ ችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተለቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱም አምባሳደሩ ለፕሬዝዳንቷ ጥያቄ አቅርበዋል ።

ክብርት ፕሬዝዳንቷም በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በአምባሳደሩ ስለቀረበላቸው ገላፃ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ችግር ለመፍታት መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚያደንቁም ተናግረዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በሚመለከትም ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ነው ሲሉም ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘውን የታንዛኒያ ኤምባሲ መሬት ጉዳይ በቅርብ መፍትሄ እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግስት ያሳለፈው ውሳኔ እንዳስደሰታቸው የተናጉሩት ፕሬዝዳንቷ የሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት ዘመን በማይሸር ወዳጅነት የተሳሰረ በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በታንዛኒያ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ዜጎች እንዲለቀቁና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ custom football jerseys nike air jordan mid cheap jordans yara ellen wille ohio state jersey wig shop detroit lions jersey intimate toys nike jordan series 06 adidas yeezy boost 350 v2 mono ice custom paintball jerseys iwona wig durex intense vibrations ring College Jerseys store personalized celtics jersey መንግስታቸው ቀና ውሳኔ እንደሚሰጥበትም አረጋግጠዋል።

ፕሬዝዳንት ሳሚያ የታንዛኒያ ዜጎች ኢትዮጵያ አቬሽን ዘርፍ ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን ያስታወሱ ሲሆን ለዚህም ኢትዮጵያ በዘረፉ ሙያ የአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን በመጥቀስ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram