Duty-Free Notes

ቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች

  • እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ፡፡

  • አገልግሎቱን ለመጠየቅ አምስት አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርብዎታል፡፡

  • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው DHL, ወይም DHL EXPRESS MAIL መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብዎትም፡፡

አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ

1)

አምስት አመትና ከዚያ ላይ በውጭ አገር መቆየትዎን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ፣ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ እና ሌላ ማስረጃ ማቅረብ

2)

ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ በሁለት ኮፒ

3)

Resident permit ካርድ በሁለት ኮፒ 

4)

መጠየቂያ ቅጽ ማመልከቻ ማስገባት

5)

የሚያስገቡት እቃዎች ዝርዝር በአንድ ኮፒ 

6)

አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (DHL, ወይም DHL EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
  

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram